Friday 6 June 2014

በኢትዮጵያ ካኦርጃ የተባለ ፅንፈኛ አመለካከትን በሀይልና በሽብር ለማስፋፋት የተንቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በኢትዮጵያ ካኦርጃ የተባለ ፅንፈኛ አመለካከትን በሀይልና በሽብር ለማስፋፋት የተንቀሳቀሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.)  በኢትዮጵያ ካኦርጃ የተባለ ፅንፈኛ የእስልምና አክራሪ አመለካከትን በሀይልና በሽብር ለማስፋፋት በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የአሸባሪ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና  የፌደራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል አስታወቀ።
ግብረ ሀይሉ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን ተጠርጣሪዎች የሽብር መረብ ለመበጣጠስ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
በቁጥር 25 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋቸውን የገለፀው ግብረ ሀይሉ፥ በሁለት የህቡዕ ቡድኖች የተደራጁት እነዚህ ተጠርጣሪዎች አልሸባብ ከተባለውና ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኑ አልቃይዳ ጋር ቁርኝት ባለው አሸባሪ ቡድን በጎረቤት አገር ሶማሊያ ግዛት ውስጥ የሽብር ስልጠና የወሰዱ ናቸው ብሏል።
አንደኛው ቡድን ቀጥተኛ አመራር የሚያገኘው ደቡብ አፍሪካ ከሚገኝ እንድ አክራሪ ቡድን እንደነበርና የሽብር ቡድኑ በሶማሊያ በአልሸባብ ስልጠና ካገኘ በኋላ በኬኒያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ አደረጃጀቱን አጠናክሮ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን እንቅስቃሴውን ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንዳለ በተደረገ ክትትል አባላቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
መግለጫው አያይዞም ሁለተኛው የሽብር ቡድን በሱዳን፣ በየመንና በኢንግሊዝ በሚገኙ ዓለም አቀፍ የካኦርጃ ጂሃዲስቶች እንቅስቃሴዎች ጋር ግኑኝነት በመመስረት  ቀትተኛ አመራርና ልዩ ልዩ ድጋፍ ሲያገኝ ቆይቷል ነው ያለው።
የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉ በክትትል የተገኘው ይህ የሽብር ቡድን 30 የሚሆኑ አባላቱን ወደ ሶማሊያ በመላክ በአልሸባብ አማካኝነት  ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረጉን ለማወቅ እንደተቻለ አስታውቋል።
የፅንፈኛው የካኦጃ እንቅስቃሴ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሀይማኖት ስም በሚፈፀሙ የሽብር ድርጊቶች ውስጥ የተጋ ተሳትፎ እንዳለው ያሳወቀው ግብረ ሀይሉ፥ እንቅስቃሴው የሚከተላቸው የእምነት መርሆዎች ከናይጄሪያው እስላማዊ አሸባሪ ቡድን ከቦኮ ሃራም እምነቶች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውን አትቷል።
ፅንፈኛ አሸባሪ ቡድኑ ጠባብ አስተምህሮውን የማይጋሩ ሌሎች ሙስሊሞችን በሙሉ በከሃዲነትና በመናፍቅነት የሚፈርጅና በከሃዲነት የፈረጃቸውን ለመግደል በፈጣሪ የተሰጠ መለኮታዊ ፈቃድ አለ የሚል አደገኛ አስተምህሮ እንደሚያራምድ መግለጫው አሳውቋል።
ንቅናቄው ለምድራዊ መንግስት ግብር መክፈልን እንደ ከፍተኛ ሀጢያትና የእምነት ጥሰት የሚመለከትና የሞባይል ካርድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚቀረጥበት በመሆኑ  በሞባይል ስልክ መገልገል በእስልምና እምነት የተከለከለ ሃጢያት /ሃራም/ ነው ብሎ የሚያራምድ ነው ብሏል መግለጫው።
የትራፊክ ህግጋትን ማክበርን ጨምሮ ዘመናዊ ትምህርትን  መሻት ወይም መከታተል ለእርግማን የሚዳርግ ከፍተኛ ሀጢያት አድርጎ በማቅረብ  ይህን አመለካከቱን በሌሎች ላይ በሀይልና በተፅዕኖ በመጫን የሚንቀሳቀስ አክራሪ አመለካከትን የሚከተል አደገኛ እንቅስቃሴ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።
ከዚህ ቀደም በ1994 ዓመተ ምህረት የካኦርጃ ታጣቂዎች በምእራብ ኢትዮጵያ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በተወሰደባቸው እርምጃ ጉዳትና ኪሳራ ደርሶባቸው እንደነበር መግለጫው አስታውሷል።
ሆኖም በቅርቡ በአክራሪ ሙስሊሞች የተሞከሩ የአመፅና የነውጥ ክስተቶች ለቡድኑ እንቅስቃሴ የሚመቹ መልካም አጋጣሚዎች ተደርገው በካኦርጃ እንቅስቃሴ አመራሮች መወሰዳቸውን ከምርመራው ለመረዳት መቻሉንም ነው ግብረ ሀይሉ  የገለፀው።
መግለጫው እንቅስቃሴው ከአገር ውጪ ከሚያገኘው የገንዘብ እርዳታ በተጨማሪ በጅማ ዞን በሚገኙ የገጠር መንገዶችና በዋና ዋና መንገዶች ላይ በሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ላይ ጥቃት በማድረስ ገንዘብና ሞባይል ሲዘርፍ መቆየቱንና በነዚህ ጥቃቶችም ሁለት ሰላማዊ ዜጎችን መግደሉን አስታውሷል።
የአሸባሪ ቡድን አባላቱ ለሽብር ድርጊቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችንና የጦር መሳሪያዎችን ሲያከማቹ መቆየታቸውን የገለፀው የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተጀመረው ምርመራ እንደተጠናቀቀም ክስ እንደሚቀርብባቸውና  ዝርዝር ጉዳዩን የሚመለከት መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚደርግ ገልጿል።
Originally Posted on: Fanabc.com

Saturday 15 February 2014

Use Reason As a Weapon

Reason is all we human beings have as a weapon. In fact the most efficient and effective weapon to destroy any enemy.

With weapons, we destroy physical entities including human beings that we perceive are threats of our existence. we destroy humans and their possessions irreplaceable. But perception is deceptive, we perceive our so called enemies unreasonably and we take mutually destructive actions simply based on emotions. And worst of all, we can never eliminate every perceived enemy.

With reason on the other hand, we destroy evil ideas, the source of all evils in this world. Evil ideas are always unreasonable. we eliminate unreasonable ideas with reason which eliminates everything.